ዛሬ የተጀመረው የመጀመርያ መንፈቅ የማጠቃለያ ፈተና በሶስቱም የሳንኮፋ ትምህርት ቤት ቅርንጫፎች

  • Home
  • ዛሬ የተጀመረው የመጀመርያ መንፈቅ የማጠቃለያ ፈተና በሶስቱም የሳንኮፋ ትምህርት ቤት ቅርንጫፎች
Shape
ዛሬ የተጀመረው የመጀመርያ መንፈቅ የማጠቃለያ ፈተና በሶስቱም የሳንኮፋ ትምህርት ቤት ቅርንጫፎች

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁንም ውስን ተግዳሮቶች በእለቱ የተስተዋሉ ሲሆን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ይቀርባሉ።

🎯 የሁለተኛ ፈረቃ ተፈታኝ ተማሪዎች መግቢያ ሰአት 3፡40 ቢሆንም ወላጆች በመጀመሩያው ፈረቃ መግቢያ ሰዓት 1:50 ተማሪዎችን ሲልኩ ተስተውለዋል። ይህም በፈተና ስርዓቱ ላይ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረድታችሁ ትምህርት ቤቱ ትላንት ባስቀመጠው የጊዜ አግባብ ብቻ ተማሪዎችን ትምህርት ቤት እንድትልኩ እና እንድትረከቡ እናሳስባለን።

🎯 ጥቂት ተማሪዎች በሁለቱም ፈረቃ አርፍደው በመምጣታቸው እራሳቸው በፈጠሩት ችግር ሲጉላሉ ተስተውለዋል። ማርፈድ መልሶ የሚጎዳው ተማሪዎችን እንደሆነ ተረድታችሁ ወላጆች ተማሪዎችን በጊዜ ውደ ትምህርት ቤት በመላክ ሃላፊነታቹሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

🎯 ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ደንብ ልብስ ላይ ተጨማሪ አልባሳት ደርበው ወደ ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ በተደጋጋሚ የገለጽን ቢሆንም አሁንም ጥቂት ተማሪዎች ልብስ ደርበው ተስተውለዋል።  ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች አለባበስ እና ፖሮቶኮል በተመለከተ ግልጽ መመሪያና ስርዓት በአመቱ መጀመሪ ያሳወቀ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የትኛውም መጉላላት ሃላፊነቱን ወላጅ እና ተማሪው እንደሚወስዱ ይገልጻል።

🎯 ከፈተና ስርዓት አግባብነት ውጪ ነጠላ ጫማ እና ሸበጥ ተጫምተው የመጡ ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን ይህም ፍፁም ክልክል እንደሆነ አውቃችሁ እንድትጠነቀቁ እናሳስባለን።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *