የሳንኮፋ መልእክት – ጥር 20 ፤ 2017

  • Home
  • የሳንኮፋ መልእክት – ጥር 20 ፤ 2017
Shape

ውድ የሳንኮፋ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ውላጆች

📌 ትምህርት ቤታችን ትምህርት ቤታችሁ የአንደኛ መንፈቅ የማጠቃለያ ፈተና በታቀደው ልክ እጅግ ባማረና የፈተና ስርዓት በተከተለ አፈፃፅም በዛሬው ቀን ለማጠቃለል ችሏል።

🎉ፈተና ተጀምሮ እስኪያበቃ ያላለሰለሰ ጥረት ስታደርጉ ለነበራችሁ እና ሃላፊነታችሁን በአግባቡ ለተወጣችሁ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች፣ወላጆች፣መምህራን እና የትምህርት ቤቱ ማናጅመንት አባላት ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ።🎉

⚠️ማሳሰቢያ⚠️

➡️ ከነገ እሮብ የሚጀምረው የተማሪዎች የፈተና ወረቀት መመለስ ፕሮግራም በ3ቱም ቅርንጫፎቻችን የሚከተለውን ይመስላል።

🎯 ታቦር፣ ወራንቻ እና ዲያስፖራ የKG ተማሪዎቻችን ውጤት የሚመለሰው ሀሙስ ጥር 22 ብቻ ሲሆን በእለቱ ውጤቱን ወላጆች በትምህርት ቤት ተገኝተው የሚረከቡ ይሆናል። ከተማሪዎች ውጤት ጋር የተያያዘ የትኝውም አይነት ቅሬታ አርብ ጥር 23 ብቻ የምናስተናግድ ይሄናል።

🎯 በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን የእንደኛ(1-8 ክፍል)  እና ሁለተኛ ደረጃ (9-12 ክፍል) ተማሪዎች ውጤት ነገ እሮብ ጥር 21 እና ሀሙስ ጥር 22 ብቻ የሚመለስ ይሆናል።

👉 ተማሪዎች ውጤት ለመቀበል ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ስትመጡ፡-

  1. በመደበኛ ትምህርት መግቢያ ሰዓት ማለትም 1:50-2:10 ከመጣችሁ ብቻ የምትስተናገዱ ይሆናል።
  2. የተማሪዎች ከትምህርት ቤት መውጫ 6:20 ይሆናል።
  3. ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ (uniform) በአግባቡ ለብሶ መገኝት የሚኖርባችሁ ሲሄን የደንብ ልብስ አሟልተቶ ያለበሰ ተማሪ ከበር የሚመለስ ይሆናል።
  4. የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከተማሪ ውጤት ጋር ተያይዞ የሚኖሩ ቅሬታዎች ከነገ እሮብ ጥር 21 እስከ አርብ ጥር 23 ብቻ የሚስተናገዱ ይሆናል።

🏵ትላንትም ዛሬም ነገም ለለውጥ እንሰራለን🏵

       🇪🇹ሳንኮፋ የኢትዮጵያ ልጆች መፍለቂያ🇪🇹

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *