ዜና ሳንኮፋ – ጥር 14 ፤ 2017

  • Home
  • ዜና ሳንኮፋ – ጥር 14 ፤ 2017
Shape
ዜና ሳንኮፋ – ጥር 14 ፤ 2017

ዛሬ ማለትም ጥር 6 2017 . በሳንኮፋ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ታቦር ቅርንጫፍ ከሚማሩ 8 እስከ 12 ክፍል  የተማሪ ተወካዮች ጋር በመጀመሪያው መንፈቅ አመት የመማር ማስተማር እና በተማሪ ባህሪ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል

 

በውይይቱ ላይ የትምህርት ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተኮላ ቸሩ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወልደዮሐንስ አጉናፍር የተገኙ ሲሆን ተወካይ ተማሪዎቹ በቀጣይ የትምህርት መንፈቅ አመት እንዲሻሻሉ እና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሏቸውን ሀሳቦች  ያነሱ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በት/ቤቱ ተዘጋጅቶ የቀረበላቸውን መጠይቅ  ሞልተዋል።

 ሳንኮፋ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ይህንን ግብዓት በመውሰድ  የትምህርት እሰጣጣችንን ለማዘመን ጥራት ያለው ትምህርት ለተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ እና ተማሪዎቻችንን በስነ ምግባር የታነፁ ይሆኑ ዘንድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለመወጣት ያለንን ቁርጠኝነት በዚሁ አጋጣሚ እየገለፅን ለመንፈቅ አመት ማጠቃለያ ፈተና የቀሩት ቀናቶች ጥቂት እንደመሆናቸው ተማሪዎች በትኩረት ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

 ተሸክመን የምንሻገረው ችግር የለም፤

ትላንትም ዛሬም ነገም ለለውጥ እንሰራለን!

ሳንኮፋ የኢትዮጵያ ልጆች መፍለቂያ! 

 

 

2 Comments

  1. Falar’s contest encourages participants to express gratitude. Gratitude has the power to strengthen the bond between students and teachers, fostering a sense of appreciation that often goes unspoken.

Leave a Reply to falar Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *